
ባሕር ዳር: ሚያዚያ 1/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እንኳን ለ1ሺህ 445ኛው ዓመተ ሂጅራ ዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ ብለዋል።
ርእሰ መሥተዳድሩ ሕዝበ ሙስሊሙ በተባረከው የረመዷን ወር እርስ በእርስ በመደጋገፍ እና በመረዳዳት እንዳሳለፈው ሁሉ ታላቁን የዒድ አልፈጥር በዓልን ሲያከበርም መልካምነት እና ደግነትን የበለጠ የሚያጸናበት፤ ለሰላም እና ለልማት በአንድነት ለመትጋት ትብብር እና ቅንጅት የሚጠናከርበት በዓል ይኾን ዘንድ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!