“ሕዝብ ተናግሯል፤ መንግሥትም ያዳምጣል” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

94

የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በወቅታዊ ጉዳይ ያስተላለፉት መልእክት። የለውጡን ስድስተኛ ዓመት በማስመልከት በሀገር አቀፍ ደረጃ በክልሎች፣ ከተማ አሥተዳደሮች እና በተዋረድ ባሉ የአሥተዳደር እርከኖች በተለያዩ ቀናት የድጋፍ ሰልፎች ተካሂደዋል። በቀሪ አካባቢዎችም ይቀጥላል። በእነዚህ ሰልፎች ሕዝቡ የሀሰት ማደናገሪያውን ጥሎ፣ እውነትን አንግቦ በጽናት ወጥቷል።

ሰላምና ደኅንነት እንዲረጋገጥ፣ የተጀመረው የብልጽግና ጉዞ እንዳይቋረጥበት፣ መልካም አሥተዳደር እንዲሰፍንና መንግሥታዊው አሥተዳደር በኀላፊነት እንዲሠራ ያለውን አቋም ገልጿል። ለውጡ ያመጣለትን የሰላም፣ የልማት፣ የዴሞክራሲ፣ የፍትሕና ራስን በራስ የማሥተዳደር መብቶች በማናቸውም ሁኔታ በሚፈጠሩ ችግሮች አሳልፎ እንደማይሰጥም አረጋግጧል።

መንግሥት የሕዝቡን ድምጽ ሰምቷል። የሰላምና ደኅንነት፤ የልማትና የመልካም አሥተዳደር፤ የወሰንና የማንነት፤ የፍትሕና የዴሞክራሲ ጥያቄዎቹን በሕግና በሥርዓት ለመፍታት ይሠራል። ሕዝብ ላሳየው የአቋም ቆራጥነት እያመሰገንኩ፣ መቼም፣ የትምና በምንም ዓይነት ሁኔታ የሕዝቡ ጥያቄዎች እንዲመለሱ መንግሥት ከሁሉም ተቀናጅቶ ሠርቶ ውጤት እንደሚያመጣ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ።

Previous article“የክልላችን ሕዝብ ለመንግሥታችን ያደረገውን ድጋፍና ለሰላም መስፈን ላሳየው ቁርጠኝነት እጅግ እናመሠግናለን” አረጋ ከበደ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር
Next article“ጽንፈኝነት የወለደው ፈተናዎች ቢገጥሙንም፣ ፈተናዎችን ወደ እድል፣ አቅማችንን ወደ ውጤት በመቀየር የብልጽግና ጉዟችንን እናስቀጥላለን” አቶ ይርጋ ሲሳይ