“የክልላችን ሕዝብ ለመንግሥታችን ያደረገውን ድጋፍና ለሰላም መስፈን ላሳየው ቁርጠኝነት እጅግ እናመሠግናለን” አረጋ ከበደ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር

66

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በአማራ ክልል የተካሄዱ የድጋፍ ሰልፎችን አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል። በበክልላች ውስጥ በሚገኙ ዞኖች፣ ከተማ አሥተዳደሮችና ወረዳዎቸ ሀገራዊ ለዉጡን የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰልፍ ተካሂዷል።

ሰላም ወዳዱ እና በችግሮችም ውስጥ ሆነ የነገዋቹን ዕድሎችና መልካም ፍሬዎች በአስተውሎት የመተንበይ ችሎታ ያለው የክልላችን ሕዝብ ያጋጠሙትን ውስጣዊ ችግሮች ተቋቁሞ አደባባይ በመውጣት ለሰላም መስፈንና ለመንግሥታችን ያለው ጥልቅ ድጋፍ በሰላማዊ የድጋፍ ሰልፍ ገልጿል።

የክልላችን ሕዝብ ሁልጊዜም እንደምንለው በችግር አረንቋ ሳይዋጥ እና በሴረኞች ሳይደናገር ለመንግሥታችን ያደረገውን ድጋፍና ለሰላም መስፈን ላሳየው ቁርጠኝነት እጅግ እናመሠግናለን።

በዛሬው እለትም የክልላችን ሕዝብ ለውጡን በመደገፍ፣ ሰላምን ለማፅናትና አብሮነትን ለማጠናከር ባደረገው ሕዝባዊ የድጋፍ ሠልፍ ላሳየው ጨዋነት እና ሰላም ወዳድነት በክልሉ መንግሥት ስም እናመሠግናለን!

በየደረጃው ለምትገኙ አመራሮች፣ የፀጥታ አካላት ሰልፉን በማስተባበርና በዕለቱ ፀጥታውን በማስከበር ለአደረጋችሁት አስተዋፅኦ የከበረ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

Previous articleMaxxansa Gaazexaa Hirkoo: Bitootessa 30/2016
Next article“ሕዝብ ተናግሯል፤ መንግሥትም ያዳምጣል” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ