
ባሕር ዳር: መጋቢት 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) “ለክልላችን ሰላም በሕብረት እንቆማለን” በሚል መሪ መልዕክት ነው ሰልፉ የተካሄደው። ሰልፈኞቹ ለሀገራቸው ሰላም እና ሁለንተናዊ ብልጽግና የበኩላቸውን እንደሚወጡ እና ሀገራቸውን ወደ ከፍታ ለማሻገር ከለውጡ መሪዎች ጋር በጽናት እንደሚቆሙ ገልጸዋል።
የድጋፍ ሰልፉ ባለፋት ዓመታት በለውጡ መንግሥት የመጡትን ማኅበራዊ፣ ፖሊቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጦችን ለመደገፍ ታሳቢ ያደረገ መኾኑ ተጠቁሟል፡፡ “እኛ ኢትዮጵያዊያን ለሀገራችን ሰላም እና ሁለንተናዊ ብልጽግና የበኩላችንን እንወጣለን፣ በጥቂት ጽንፈኛ ኃይሎች አስተሳሰብ እና እኩይ ድርጊት የሚበተን ሀገር እና ሕዝብ የለንም፣ ሀገራችንን ወደ ከፍታ ለማሻገር ከለውጡ መሪዎች ጋር በጽናት እንቆማለ”! የሚሉ እና ሌሎችም መፈክሮች ተሰምተዋል።
መረጃው፡- የሐራ ከተማ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ነው፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!