
ባሕር ዳር: መጋቢት 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በደቡብ ወሎ ዞን አልብኮ ወረዳ ሳልመኔ ከተማ ሀገራዊ ለውጡን የሚደግፍ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል።,ሠልፈኞቹ ባሰሙት መልእክት እንዳሉት ኢትዮጵያ የዓድዋ ድልን ዳግም እያደሰች የምትገኝበት ጊዜ ላይ እንደኾነች ተናግረዋል፡፡
የላቀ ሕዝባዊ ተሳትፎ ለኢትዮጵያዊያን ብልጽግና ወሳኝ እንደኾ ያስረዱት ሠልፈኞቹ በክልሉ ያለውን አንጻራዊ ሰላም በአጭር ጊዜ ወደ ዘላቂ ሰላም ለማሽጋገር ከለውጡ አመራር ጋር በጋራ እንደሚሠሩ ነው ያብራሩት፡፡ ሀገራዊ ለውጡ ኢትዮጵያውያንን የታደገ እና ህልውናን ማስቀጠል ያስቻለ እንደኾነም አስገንዝበዋል፡፡
እንደ አልብኮ ወረዳ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት መረጃ ክልሉን በውክልና ጦርነት ማፍረስ አይቻልም የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶችም በሠልፈኞቹ ተስተጋብተዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!