
ባሕር ዳር: መጋቢት 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ጎንደር ዞን በላይ ጋይንት ወረዳ እና ነፋስ መውጫ ከተማ አሥተዳደር “ለሰላማችን ዘብ እንቆማለን ለውጡን እናጸናለን!” በሚል መሪ ሃሳብ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል።
ከክልሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የሰልፉ ተሳታፊዎች ባለፉት ስድስት ዓመታት በሀገሪቱ በለውጡ የተገኙ ስኬቶችን የሚደግፉ የተለያዩ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!