
ደሴ: መጋቢት 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በቃሉ ወረዳ ደጋን ከተማ ስኬቶችን የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰልፍ ነው የተካሄደው። በሰልፉ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የቃሉ ወረዳ ምክትል ዋና አሥተዳደሪ ሙህዲን አህመድ ሁሌም ለሚደግፉን የወረዳችን ነዋሪዎች አክብሮታችን ከፍ ያለ ነው ብለዋል።
ዋና አሥተዳዳሪው አክለውም ክልላችንን በውክልና ጦርነት እየወጋ ያለው ጽንፈኛ ኃይል እንዲወገድ የወረዳችን ሕዝብ እና መንግሥት አምርሮ የሚታገለው መኾኑን ገልጸዋል።
በወረዳው የተጀመሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል ፡፡ ዋና አሥተዳዳሪው ለውጡ ሀገሪቱን ከፍ ባደረጉ ታላላቅ ሥራዎች እና ኅብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት ከፍ ብሎ አንድነት የደመቀበት እና በቃሉ ወረዳም የተለያዩ ፕሮጀክቶች የተጀመሩበት እንደኾነ አስረድተዋል፡፡
ሠልፈኞቹ በመስኖ ያለሙትን የተለያዩ የበቆሎ እና የሙዝ ምርት ሰልፉ ላይ ይዘው ወጥተዋል።
ሰልፈኞቹ እንደ ወረዳ እና ዞን በርካታ ለውጦች ተመዝግበዋል ነው ያሉት። የሰላሙን እና የኑሮ ውድነቱን ችግር ለመፍታት ከመንግሥት ጎን በመቆም የበኩላችንን ድርሻ እንወጣለን ብለዋል። በመጨረሻም ዋና አሥተዳዳሪው ከቀናት በኋላ ለሚከበረው የዒድ አል ፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ፡- አንተነህ ፀጋዬ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!