
ባሕር ዳር: መጋቢት 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በድጋፍ ሰልፉም የምዕራብ ጠለምት ወረዳ እና የማይጠምሪ ከተማ ሕዝብ አደባባይ ወጥቶ መልዕክቱን አስተላልፏል፤ ጥያቄውንም አቅርቧል። በሰልፉ ላይ የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ዲያቆን ሸጋው ውቤን ጨምሮ የዞን አመራሮች፣ የከተማ እና የወረዳ አመራሮች፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት የ501ኛ ኮር አመራሮች፣ የአካባቢዉ የፀጥታ አካላት ተገኝተዋል።
አደባባይ ወጥቶ ድጋፉን የገለጸው ሕዝብ ጥያቄዎቹን እና መልዕክቱንም በጨዋ ደንብ አቅርቧል፤ አቋሙን እና እውነቱንም ለዓለም አሳውቋል። በድጋፍ ሰልፉ ላይ ክብርና ምስጋና ነጻ ላወጣን ጥምር ጦራችን፣ የአማራ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ለጠለምት ሕዝብ ነጻነት ለከፈላችሁት መስዋዕትነት እናመሰግናለን፣ በማንነታቸው ምክንያት በትግራይ ኃይሎች የታሰሩ የጠለምት አማራዎች ይፈቱልን፣ የጠለምት የማንነት ጥያቄ ለኢትዮጵያ ከፍታ መሠረት ነው፣ እኛ የጠለምት አማራዎች ልማት እንጅ ጦርነትን አንፈልግም፣ የፕሪቶሪያው ስምምነት ይከበርልን! የማንነት ጥያቄያችን ይመለስልን የሚሉጥያቄዎች እና መልዕክቶች ተሰምተዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!