
ደሴ፡ መጋቢት 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) “ለክልላችን ሰላም በኅብረት እንቆማለን” በሚል መሪ መልዕክት በደሴ ከተማ የድጋፍ ሠልፍ ተካሄደ።
በድጋፍ ሰልፉ የተለያዩ መልእክቶች ተላልፈዋል። ሰልፈኞቹ ከያዟቸው መልእክቶች መካከል፦
👉እኛ ኢትዮጵያዊያን ለሀገራችን ሰላም እና ሁለንተናዊ ብልጽግና የበኩላችንን እንወጣለን፣
👉ሀገራችንን ወደ ከፍታ ለማሻገር ከለውጡ አመራር ጋር በጽናት እንቆማለን!፣
👉ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የአንድነታችን እና የጥንካሬአችን መገለጫ ነው!፣
👉በገበታ ለሸገር የጀመርነውን፤ በገበታ ለሀገር እንደግመዋለን!!!
👉 የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ድል እና ስኬት የአባቶቻችንን ገድል የደገምንበት ታሪካዊ አሻራ ነው፣
👉 ውስጣዊ ሠላማችንን በማጽናት ውጫዊ ተፅዕኖዎችን በድል እንወጣለን!!!
👉የክልላችንን አንጻራዊ ሠላም በአጭር ጊዜ ወደ ዘላቂ ሠላም እናሸጋግረዋለን!!
እነዚህ እና መሰል የድጋፍ መልእክቶች ተላልፈዋል። የደሴ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ ፍቅር እና ሰላምን ሸምና የኖረችው የፍቅር ከተማዋ ደሴ ለዘመናት የናፈቃትን ልማት እያገኘች ያለችዉ የለውጥ አመራሩ ከሕዝቡ ጋር ተናቦ በመሥራቱ ነው ብለዋል።
የሕዝቡ የዘመናት ጥያቄ በልማቱ ዘርፍ እየተመለሰለት መኾኑንም አንስተዋል። የጤና የትምህርት እና የመሰረተ ልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መኾናቸውን በመግለጽ፡፡
ሕዝቡ ችግሮችን ተሻግሮ በማለፍ የበቃ መርከበኛ መኾኑን አሳይቶናል ብለዋል በንግግራቸው። የሰላም አምባሳደር ለኾነዉ ለደሴ ከተማ ሕዝብ የላቀ ምስጋናቸዉንም አቅርበዋል ከንቲባው። ጠላቶቻችን እኛን እርስ በርስ እስከ ወድያኛው የማይግባባ ማኅበረሰብ አድርጎ ለመፍጠር የሚሠሩብንን ሴራ ሕዝቡ ከመንግሥት ጎን ኾኖ ሊታገለዉ ይገባል ብለዋል፡፡
ላለፋት ዓመታት እዉቅና ተነፍጓቸዉ የነበሩ የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች በለውጡ መንግሥት ቀርበዉ እንዲታዩ እና መፍትሔ እንዲያገኙ እየተሠራ መኾኑም መዘንጋት የለበትም ብለዋል። “ክልሉ በኢኮኖሚ እንዲደቅ እና ሕዝቡ በኑሮ ውድነት እንዲሰቃይ እያደረገ ያለዉን ዘራፊ ቡድን መታገል አለብን” ብለዋል ከንቲባው፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!