
ባሕር ዳር: መጋቢት 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ሰልፉ ላይ ለክልላችን ሰላም በሕብረት እንቆማለን፣ በጥቂት ጽንፈኛ ኃይሎች አስተሳሰብ እና እኩይ ድርጊት የሚበተን ሀገር እና ሕዝብ የለንም፣ ክልላችንን በውክልና ጦርነት ማፍረስ አይቻልም፣ እኛ ኢትዮጵያዊያን ለሀገራችን ሰላም እና ሁለንተናዊ ብልጽግና የበኩላችንን እንወጣለን የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶች ተላልፈዋል።
በተጨማሪም ሀገራዊ ለውጡ ኢትዮጵያን የታደገ እና ህልውናችንን ያስቀጠለ ነው፣ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የአንድነታችን እና የጥንካሬችን መገለጫ ነው፣ ውስጣዊ ሰላማችንን በማጽናት ውጫዊ ተፅዕኖዎችን በድል እንወጣለን፣ የክልላችንን አንጻራዊ ሰላም በአጭር ጊዜ ወደ ዘላቂ ሰላም እናሸጋግረዋለን የሚሉ ድምጾችም ተሰምተዋል፡፡
የሰልፉ ተሳታፊዎች ጉድለቶችን በማረም በለውጡ የተገኙ ድሎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ከለውጡ መሪዎች ጋር በጽናት መቆም እንደሚገባም አመላክተዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!