በሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ቀያ ገበርኤል ወረዳ ሕዝባዊ ሰልፍ ተካሔደ፡፡

31

ባሕር ዳር: መጋቢት 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በሰልፉ ላይ የዘመሮ ከተማ ነዋሪዎች፣ የመንግሥት ሠራተኞች እና የገጠር ቀበሌዎች ተሳትፈውበታል። በሰልፉም ላይ በጽንፈኞች እና ተላላኪዎች ምክንያት የሚፈርስ ክልልም መንግሥትም የለም፣ ሀገራችንን ለማስቀጠል ከለውጡ አመራር ጎን እንቆማለን፣ ኢትዮጵያ ዳግም የዓድዋን ድል እየደገመች ነው፣ ሰላማችን በእያንዳንዳችን ቤት ናት የሚሉ መልእክቶች በሰፊው ተላልፈዋል።

በመጨረሻም የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሸዋመነ ኃይሌ መልእክት ያስተላለፉ ሲኾን የወረዳችን ሕዝብ ለፍቶ አዳሪ ሰላም ወዳድ ለሰላም ዘብ የሚቆም ነው ብለዋል፡፡ ነገር ግን ከሕዝቡ ጉያ የወጡ ጽንፈኛ ኃይሎች ሕዝባችንን ሰላሙን እየነሱት ይገኛሉ፡፡ በመኾኑም መላ የወረዳችን ማኅበረሰብ ጽንፈኛውን “በቃ ሰላም እንፈልጋለን” ያለበትን አካሔድ አጠናክሮ በመቀጠል ለሰላሙ ዘብ ሊቆም ይገባል ብለዋል።

የወረዳው ዋና አሥተዳዳሪ ሸዋይርጋ ተክለወልድ በበኩላቸው ሰላም አንዴ ከእጃችን ካመለጠን መልሰን ለማግኘት ከፍተኛ መስዋእትነት ያስከፍላል፤ ስለኾነም ለሰላማችን ዘብ ልንቆም ይገባል ብለዋል፡፡ መላ የወረዳችን ማኅበረሰብ ይህንን የጽንፈኛ አስተሳሰብ በቃ ብሎ ሊያስወግድ ይገባል ብለዋል።
መረጃው፡- የመንዝ ቀያ ምድር ወረዳ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ ሀገራዊ ለውጡን የሚደግፍ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
Next articleበደቡብ ወሎ ዞን በወረባቦ ወረዳ ሀገራዊ ለውጡን የሚደግፍ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በቢስቲማ ከተማ ተካሂዷል፡፡