
ደሴ: መጋቢት 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ ደጋን ከተማ ውስጥ ሀገራዊ ለውጡን የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው፡፡ በድጋፍ ሰልፉ ላይ ለክልላችን ሰላም በኅብረት እንቆማለን፤ ለሀገራችን ብልፅግና ዕውን መኾን እንተጋለን፤ በጋራ ጥረት ሰላማችንን እናረጋግጣለን፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የአንድነታችን እና የጥንካሬችን መገለጫ ነው፤ ዉስጣዊ ሰላማችንን በማፅናት ዉጫዊ ተፅዕኖዎችን በድል እንወጣለን፤ የክልላችንን አንፃራዊ ሠላም በአጭር ጊዜ ወደ ዘላቂ ሰላም እናሸጋግረዋለን እና የመሳሰሉት መልእክቶች ተስተጋብተዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!