በሰቆጣ ከተማ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

28

ሰቆጣ: መጋቢት 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ሰቆጣ ከተማ ባለፉት አምስት ዓመታት የተሠሩ የልማት ጅማሮዎችን የሚደግፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው። በድጋፉ ላይ የሰቆጣ ከተማና የአጎራባች ቀበሌዎች ነዋሪዎች፣ የብሔረሰብ አሥተዳደሩ የሥራ ኀላፊዎች እና የሃይማኖት አባቶች እየተሳተፉ ነው።

ሰላማችን በቤታችን ናት፣ ሃገራዊ ለውጡ ኢትዮጵያን የታደገ እና ህልውናችንን ማስቀጠል ያስቻለ ነው፤ በጥቂት ጽንፈኛ ኃይሎች አስተሳሰብ እና እኩይ ድርጊት የሚበተን ሀገር የለም፤ ቅድሚያ ለሰላማችን እንሰጣለን፤ ለሀገራችን ሰላም እና አንድነት የማንከፍለው ዋጋ አይኖረንም እና የመሳሰሉ መልእክቶች በድጋፍ ሰልፉ ላይ ተስተውለዋል።

ዘጋቢ:- ደጀን ታምሩ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየመገጭ ግድብ ቀጣይ እጣ ፋንታው ምንድን ነው?
Next articleበምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳውኃ ከተማ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።