ምሥጋና 🙏

49

የፊደል ገበታ አባት- ቀኝ አዝማች ተስፋ ገብረሥላሴ!

👉በ1895 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ ቡልጋ ውስጥ አክርሚት በተባለ ስፍራ ተወለዱ።

👉የቤተ ክርስቲያን መምህር ከነበሩት ከአባታቸው ገብረሥላሴ ቢልልኝ እግር ስር ተቀምጠው ፊደል ቆጥረዋል።

👉የኢትዮጵያውያን ባለውለታ የሚያደርጋቸውን የፊደል ገበታ አዘጋጅተዋል።

👉የአማርኛ የፊደል ሆሄያትን በገጠሪቱ የኢትዮጵያ ክፍል እየዞሩ ለማኅበረሰቡ በማስተማርም ይታወቃሉ።

👉በገጠሩ ያለው ማኅበረሰብ “የፊደል አባት” ሲላቸው ምሁራን ደግሞ “የፊደል ገበታ አባት” ይሏቸዋል።

👉የፍየል ቆዳ በእንጨት ላይ በመወጠር እየፋቁ ቀለም ከልዩ ልዩ እፅዋት እያነጠሩ እና ፊደላትን በመቃ ብዕር እየጻፉ በማራባት ለወገናቸው የዕውቀት ማደግ ትልቅ አበርክቶን ተወጥተዋል።

👉በ1921 ዓ.ም ማተሚያ ቤት በማቋቋም “ዕውቀት ይስፋ፤ ድንቁርና ይጥፋ፤ ይህ ነው የኢትዮጵያ ተስፋ” በሚል ፊደልን፣ ፊደለ ሐዋርያን እና አቡጊዳን በሦስት ረድፎች እያዘጋጁ በማሳተም በመላ ኢትዮጵያ አሰራጭተዋል።

👉ኢትዮጵያውያንን በተለይም በገጠራማ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎችን ከፊደላት ጋር እንዲተዋወቁ አስችሏል።

👉ቀኝ አዝማች ተስፋ ገብረሥላሴ በፋሽስት ጣሊያን ወረራ ጊዜም ሕዝብን የሚያነቃቁ ጹሑፍ በማሰራጨት ለሀገራቸው ታግለዋል፤ አታግለዋል።

👉የፊደል ገበታን ቀርጸው መሃይምነትን ለማጥፋት ካበረከቱት አስተዋፅኦ በተጨማሪ በአርበኝነት ትግላቸው ላደረጉት ተጋድሎም የቀኝ አዝማችነት ማዕረግም ተሰጥቷቸዋል።

👉ቀኛዝማች ተስፋ ገብረሥላሴ ከእፅዋት የቀለም ዱቄት ቀምመው እና በጥብጠው፣ ከመቃ እንጨት ብዕር ቀርጸው በወረቀት ላይ ፊደል በመጻፍ ሚሊዮኖችን ከመሃይምነት ያወጡና የዕውቀትን ብርሃን የፈነጠቁ ታላቅ አበርክቶም ያላቸው አባት ናቸው።

የመረጃ ምንጮቻችን “ዘመን ተሻጋሪ ባለ-ውለታ” የታሪክ መጽሐፍ እና ከኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር ናቸው።

Previous articleበሩዋንዳ ኪጋሊ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሕንጻ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።
Next article“ጽንፈኝነት እያደገ ሲመጣ ራስን ይበላል” አቶ ደሳለኝ ጣሰው