ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በሰመራ እየተካሄደ ነው።

22

ባሕር ዳር: መጋቢት 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ሀገራዊ ለውጡን የሚደግፍ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በአፋር ክልል ሰመራ እየተካሄደ ነው፡፡

ሰልፉ ላይ “እኛ ኢትዮጵያዊያን ለሀገራችን ሠላም እና ሁለንተናዊ ብልፅግና የበኩላችንን ድርሻ እንወጣለን″፣ በጥቂት ፅንፈኛ ኃይሎች አስተሳሰብ እና እኩይ ድርጊት የሚበተን ሀገር እና ሕዝብ የለም″፣ ″የላቀ ሕዝባዊ ተሳትፎ ለኢትዮጵያ ብልፅግና” የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶች ተላልፈዋል፡፡

በተጨማሪም “ሀገራዊ ለውጡ ኢትዮጵያን የታደገ እና ህልውናችንን ያስቀጠለ ነው″፣ ″ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የአንድነታችን እና የጥንካሬችን መገለጫ ነው″፣ ″ሠላማችን በእያንዳንዳችን ቤት ናት” የሚሉ ድምጾችም ተሰምተዋል፡፡

ሰልፈኞቹ ለውጡ ኢትዮጵያን ትክክለኛ የፌዴራሊዝም ሥርዓት ያጎናጸፈ መኾኑን በመግለጽ የአፋር ሕዝብ ከለውጡ ወዲህ የሚገባውን የፖለቲካ ውክልና ማግኘቱን ተናግረዋል፡፡

ኢቢሲ እንደዘገበው የሰልፉ ተሳታፊዎች ጉድለቶችን በማረም በለውጡ የተገኙ ድሎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ከለውጡ መሪዎች ጋር በፅናት መቆም እንደሚገባም አመላክተዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በአሶሳ እየተካሄደ ነው።
Next articleአዲስ አበባ እና የሩዋንዳ ርእሰ መዲና ኪጋሊ የእህትማማች ከተማነት ስምምነት ተፈራረሙ።