
ባሕር ዳር: መጋቢት 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ሀገራዊ ለውጡን የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰልፍ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
በድጋፍ ሰልፉ ላይ ″ሠላማችን በእጃችን ነው″፣ ለሀገራችን ብልፅግና እውን መኾን እንተጋለን″፣ ″በጋራ ጥረት ሰላማችንን እናረጋግጣለን″ የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶች በመተላለፍ ላይ ይገኛሉ፡፡
ሰልፉ ላይ የከተማው ነዋሪዎች፣ የመንግሥት ሠራተኞች፣ ባለሃብቶች እና የንግዱ ማኅበረሰብን ጨምሮ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ መኾናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!