“የሕዝብን የኢኮኖሚ እና የሰላም ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ታሪካዊ አደራ ተጥሎባችኋል” አቶ ደሳለኝ ጣሰው

54

ባሕር ዳር: መጋቢት 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ) መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ የቀድሞው የአማራ ልዩ ኃይል አባላት ሁለተኛ ዙር ሰልጣኞች ተመርቀዋል።

የቀድሞው የአማራ ልዩ ኃይል አባላት በብር ሸለቆ የውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የተሐድሶ ስልጠናቸውን አጠናቅቀው ተመርቀዋል።

በምርቃ ስነ ሥርዓቱ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአስተዳደር ጉዳዮች አስተባባሪ እና የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ ደሳለኝ ጣሰው፣ የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደስዬ ደጀንን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች እና የሀገር መከላከያ ሠራዊት የጦር መኮንኖች ተገኝተዋል።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ መልእክት ያስተላለፉት በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአስተዳደር ጉዳዮች አስተባባሪ እና የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ ደሳለኝ ጣሰው የሕዝብን የኢኮኖሚ እና የሰላም ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ታሪካዊ አደራ ተጥሎባችኋል ብለዋቸዋል። የተጀመረውን ሰላም ለማጽናት ጠንክረው እንዲሠሩም አሳስበዋል።

የተሐድሶ ስልጠናቸውን አጠናቅቀው የተመረቁ የቀድሞ የአማራ ልዩ ኃይል አባላትም ሕዝባቸውን ለመጠበቅ እና ለመካስ ዝግጁ መኾናቸውን ተናግረዋል።

በመጀመሪያ ዙር የተሐድሶ ስልጠና የወሰዱት የቀድሞው የአማራ ልዩ ኃይል አባላት የክልሉን ሰላም ለማረጋገጥ ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረጉ መኾናቸው ይታወቃል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበግድቡ ኢትዮጵያ ያካበተችው ልምድ እና የዲፕሎማሲ ችሎታ በቀጣይ በሚገነቡ ሌሎች ግድቦች ሊገጥሙ የሚችሉ ፈተናዎችን ለማለፍ እገዛ እንደሚያደርግ የውኃ ፖለቲካ ተመራማሪው ያዕቆብ አርሳኖ (ዶ.ር) ተናገሩ፡፡
Next articleሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በአሶሳ እየተካሄደ ነው።