
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የሲዳማ የዘመን መለወጫ የኾነው “ፊቼ ጫምባላላ” በዓል በሀዋሳ ከተማ የፍቅር ሀይቅ ዳርቻ በሚገኘው ‘ሶሬሳ ጉዱማሌ’ እየተከበረ ነው።
የ”ፊቼ ጫምበላላ” በዓል አብሮነትን፣ ሰላምን እና መረዳዳትን በሚያጠናክሩ ክንውኖች ታጅቦ ነው እየተከበረ የሚገኘው።
በዓሉ የሲዳማ ባሕላዊ ጭፈራ በኾነው ‘ቄጣላ’ ጨዋታ እና በተለያዩ ባሕላዊ ክዋኔዎች ታጅቦ እየተከበረ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
በበዓሉ ላይ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎችን ጨምሮ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ወጣቶች ታድመዋል።
የሲዳማ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኀላፊ ወሰንየለህ ሰምኦን በዓሉ ወደ አዲሱ ዓመት የመሸጋገሪያ ብሥራት ነው ብለዋል።
ኢዜአ እንደዘገበው በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ከፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅተው እየሠሩ መኾናቸውን አመላክተዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!