“የዲጂታል የፋይናንስ ሥርዓት ተጠቃሚዎች ቁጥር ከፍተኛ ዕድገት እያስመዘገበ ነው” የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ

32

ባሕር ዳር: መጋቢት 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱን ጨምሮ የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም ኀላፊዎች እና ተወካዮች በተገኙበት የኢትዮጵያ ዲጂታል ፋይናንስ ሥርዓት የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
መድረኩ የተዘጋጀው በኢትዮጵያ የዲጂታል ፋይናንስ ስትራቴጂክ ተደራሽነት፣ ደኅንነት እና ቅልጥፍና በዘርፉ የመጡ ለውጦች ላይ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ በማለም ነው።

የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ እንዳሉት የዲጂታል ፋይናንስ ሥርዓት ለአካታች ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የማይተካ ሚና አለው። ይህንንም ተከትሎ መንግሥት ለአካታች የዲጂታል ፋይናንስ ምህዳር መጎልበት አስፈላጊ የቴክኖሎጂ ልማት ሥራ እያከናወነ መኾኑን ገልጸዋል።
አሁን ላይ የዲጂታል ፋይናንስ ሥርዓት ከፍተኛ ዕድገት እያስመዘገበ መኾኑንም ጠቁመዋል።

ኢዜአ እንደዘገበው የሞባይል ባንኪንግ፣ የኤቲ ኤም እና መሰል የዲጂታል የፋይናንስ ሥርዓት ተጠቃሚዎች ቁጥርም ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍተኛ ዕድገት እያስመዘገበ መኾኑንም አንስተዋል። ብሔራዊ ባንክም በቀጣይ ለዲጂታል ፋይናንስ ሥርዓት ዕድገት የሚያግዙ ገንቢ ምክረ ሃሳቦችን ተግባራዊ ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሠራ አረጋግጠዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሕዝቡ ጦርነት በቃን ብሎ ወደ ልማት በመመለስ ለሰላም ዋጋ መክፈል እንዳለበት የሰሜን ጎንደር ዞን ገለጸ፡፡
Next article“ዲያስፖራው በሀገር ውስጥ ልማት ተሳታፊ እንዲኾኑ ምቹ ሁኔታ መፍጠር ያስፈልጋል” አቶ ዳንኤል ደሳለኝ