ዘላቂ እና አስተማማኝ ሰላምን ለማስፈን ከመንግሥት ጋር ተቀናጅተው እንደሚሠሩ የሰከላ ወረዳ ነዋሪዎች ገለጹ።

20

ፍኖተ ሰላም: መጋቢት 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ዘላቂ እና አስተማማኝ ሰላምን ለማስፈን ከመንግሥት ጋር ተቀናጅተው እንደሚሠሩ በምዕራብ ጎጃም ዞን የሰከላ ወረዳ ነዋሪዎች ገልጸዋል። በወረዳው ግሽ ዓባይ ከተማ ከገጠር ቀበሌዎች ከተወጣጡ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር በወቅታዊ የሰላም ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።

በተደጋጋሚ በሚፈጠሩ የፖለቲካ እና የፀጥታ ችግሮች ከልማት ተነጥለናል ያሉት የሰከላ ወረዳ ነዋሪዎች በቀጣይ ዘላቂና አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን የድርሻቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።

ነዋሪዎቹ በፀጥታ ችግር ምክንያት የተቋረጠው የአስፋልት መንገድ እና ሌሎች የመሰረተ ልማት ግንባታ ሥራዎች ተመልሰው እንዲጀመሩላቸው ጠይቀዋል። በሁሉም የልማት መስክ ከመንግሥት ጋር ተቀናጅተው እንደሚሠሩም ነዋሪዎች አረጋግጠዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ከሰሞኑ በትግራይ ክልል በኩል በአማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የሚታየው አዝማሚያ ተገቢነት የሌለው ብቻ ሳይኾን የፕሪቶሪያውን ስምምነት የሚጥስ ነው” ለገሰ ቱሉ (ዶ.ር)
Next articleቀጣይ እጣ ፋንታው ምንድን ነው?