
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በጉባኤው የከተማዋን የመልካም አሥተዳደር ሥርዓት ለማሻሻል፣ የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ፣ ካለፉት ወራት አፈጻጸም በመነሳት እንደሚገመግም እና የቀጣይ ጊዜ የትኩረት አቅጣጫዎችን እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል።
ምክር ቤቱ የከተማ አሥተዳደሩን የ6 ወር ሥራ አፈጻጸም፣ የደንብ ማስከበር መምሪያ፣ የኦዲት ሪፖርት እና የባሕር ዳር ስማርት ሲቲ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ማቋቋሚያ ደንብ ገምግሞ እንደሚያጸድቅም ይጠበቃል።
የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው የከተማ አሥተዳደሩን የ2016 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት በማቅረብ ላይ ናቸው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!