
አዲስ አበባ: መጋቢት 24/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በታላቁ የሕዳሴ ግድብ የ13ኛ ዓመት የአከባበር በዓል ላይ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ማስታወሻነት የተዘጋጀው ቴምብር ነው የተመረቀው።
በታላቁ የሕዳሴ ግድብ የ13ኛ ዓመት የአከባበር በዓል ላይ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት የተዘጋጀ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ማስታወሻ ቴምብርን መርቀው ይፋ አድርገዋል።
በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ላይ የታተመው ቴምብርም በ192 ሀገራት ላይ ይሠራጫል ነው የተባለው።
ዘጋቢ፡- ራሔል ደምሰው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!