ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተወያዩ።

74

ባሕር ዳር: መጋቢት 23/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር መወያየታቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አሳውቀዋል። የውይይቱ የመጀመሪያው ዓላማ ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ ተግባራት ላይ አስተያየቶች እና ትችቶችን ማሰባሰብ መኾኑንም ገልጸዋል። ውይይቱ ለፖሊሲ ግብዓት አስፈላጊ የኾኑ እርማቶችን እና ማስተካከያዎችን በመለየት፣ ወደፊት ለመቀጠል በሚያስፈልገው የትብብር ዓይነት ላይ ለመመካከር ያለመ ስለመኾኑም ጠቅሰዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleአገልግሎት አሠጣጡ እንዲሻሻል እና የመልካም አሥተዳደር ችግሮች እንዲቀረፉ የግሽ ዓባይ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ጠየቁ።
Next articleበአማራ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ክልላዊ ኮንፈርንስ ከመጋቢት 21 እስከ 23/2016 ዓ.ም ድረስ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በባሕር ዳር ከተማ “ቃልን በተግባር ለኢትዮጵያ ብልፅግና!” በሚል መሪ መልእክት ሲካሄድ ቆይቶ ባለ 7 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።