
ባሕር ዳር: መጋቢት 23/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ጎንደር ዞን በስማዳ ወረዳ የማዳበሪያ ስርጭት እየተካሄደ መኾኑን የወረዳው ግብርና ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡ ለ2016/17 የምርት ዘመን ከ60 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት በሰብል የሚሸፈን መኾኑንና ለዚህ ደግሞ 80 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለማስገባት እየሠራ እንደሚገኝም ተገልጿል።
ለአርሶ አደሩ የአፈር ማዳበሪያ ማሰራጫ ኩፖን በማዘጋጀት በ1ኛ እና 2ኛ ዙር የገባውን ማዳበሪያ ቅድሚያ ወደ ዘር ለሚገቡ ደጋማ ቀበሌዎች እየተሰራጨ ነው ብሏል ጽሕፈት ቤቱ። በእቅድ የተያዘውን የአፈር ማዳበሪያ ሙሉ በሙሉ ወደ ወረዳው ለማስገባት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርበት እየተሠራ መኾኑን ከወረዳው መንግሥት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!