
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በምሥራቅ ጎጃም ዞን የስናን ወረዳ ነዋሪዎች ከቀጣናው ኮማንድ ፖስት ጋር መክረዋል፡፡ በምክክሩ ነዋሪዎቹ ጽንፈኛው ቡድን በደል እና ግፍ እንዳደረሰባቸው ተናግረዋል። መንግሥት ከዚህ በፊት የነበሩትን የመልካም አሥተዳደር ችግሮች በመፍታት ሕዝቡን በቅንነት እንዲያገለግል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ሰላም፣ ልማት እና ሠርቶ መኖር ስለሚፈልጉ መንግሥት የሕግ የበላይነት እንዲኖር ማድረግ አለበት ብለዋል።
የስናን ወረዳ ኮማንድ ፖስት ሠብሣቢ እና የክፍለጦሩ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ሌተናል ኮሎኔል አለምሰገድ ተስፋየ እንደተናገሩት ሠራዊቱ ለሕዝቡ ዘላቂ ሰላም ሲል የማይከፍለው መስዋዕትነት እንደሌለ ገልጸዋል፡፡
የጎጃም ኮማንድፖስት ለአሚኮ በላከው መረጃ በቀጣይም የሰላም ጸር የኾነውን ጽንፈኛ ከገባበት በመግባት ሕግ ለማስከበር እና የሕዝብን ሰላም ለመመለስ ጠንክረው እንደሚሠሩም አረጋግጠዋል።
የስናን ወረዳ አመራሮችም፣ መንግሥት የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ በቁርጠኝነት እየሠራ መኾኑን እና ኅብረተሰቡም ከመንግሥት የፀጥታ ኀይሎች ጎን እንዲቆም አሳስበዋል፡፡ ኅብረተሰቡም መረጃ በመስጠት በጋራ መታገል እንዳለበት ተናግረዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!