“ጠንካራ ፓርቲ እና ጠንካራ አመራር በመፍጠር ለሕዝብ መሥራት ያስፈልጋል” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ

30

ባሕር ዳር፡ መጋቢት 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት “ቃልን በተግባር ለኢትዮጵያ ብልጽግና” በሚል መሪ መልእክት ክልላዊ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በኮንፈረንሱ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት ኮንፈረንሱ ባለፉት ሁለት ተኩል ዓመት የፓርቲ አባላት ሕዝብን ለማገልገል የተወጧቸውን ዝርዝር ተግባራት የምናይበት ይኾናል ብለዋል። የሚያደናግሩ አስተሳሰቦች የሚጠሩበት ለወደፊትም በጥንካሬ ሕዝብን ለማገልገል ቀጥ ያለ አቋም የሚያዝበት ኮንፈረንስ እንደሚኾንም ገልጸዋል።

ርእሰ መሥተዳድሩ “ሕዝባችን ዋጋ የሚከፍለው ጠንካራ የመንግሥት አካል ሲያጣ ነው፤ ጠንካራ ፓርቲ እና ጠንካራ አመራር በመፍጠር ለሕዝብ መሥራት ያስፈልጋል” ሲሉም አስገንዝበዋል። ጠንካራ አመራር ከሌለ ሕዝባችን የሚመኘውን ነገር ማግኘት ይቅርና በእጁ ያለውን ልማትም ያጣል ሲሉ ተናግረዋል።

ርእሰ መሥተዳድሩ በክልሉ የተፈጠረው የሰላም እጦት የክልሉን ሕዝብ ከምንጊዜውም የበለጠ ዋጋ አስከፍሏል ብለዋል። “ከተግባር መማር አለብን፤ እንዲህ አይነት ምስቅልቅል በሕዝባችን ላይ እንዳይደርስ ቆርጠን መሥራት ይኖርብናል” ሲሉም አስገንዝበዋል። ርእሰ መሥተዳድሩ ወቅቱ አስተዋይ የኾነ አመራር እና ፓርቲ የሚያስፈልግበት ነው ብለዋል። ሁሉም መሪዎች በብርታት በመሥራት እና የተገኙ እድሎችን በሙሉ ለሕዝብ ጥቅም በማዋል ጠንካራ ፓርቲ እና ሀገር በመገንባቱ ረገድ ጎልቶ መውጣት አለባቸው ሲሉም አስገንዝበዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የጸጥታው ችግር የኅብረተሰቡን ተጠቃሚነት እንዳናረጋግጥ አድርጎናል” የመስኖ እና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ
Next article