
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ክልል አቀፍ ኮንፈረንሱን በባሕር ዳር ከተማ ማካሔድ ጀምሯል። ኮንፈረንሱ ከመጋቢት 21/2016 ዓ.ም እስከ መጋቢት 23/2016 ዓ.ም “ቃልን በተግባር ለኢትዮጵያ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል ነው የሚካሄደው።
በኮንፈረንሱ ላይ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ እንዲሁም የክልል፣ የዞን እና የወረዳ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ይገኛሉ። በተጨማሪም የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች እና አባላት በኮንፈረንሱ ላይ ተሳታፊ ናቸው። ዛሬን ጨምሮ ለሦስት ቀናት በሚካሄደው መድረክ ባለፋት ሁለት ተኩል ዓመታት የክልሉን ሕዝብ ተጠቃሚ ለማድረግ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ተነስተው በጥንካሬ እና ውስንነቶች ላይም ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል።
በኮንፈረንሱ ስለክልሉ አጠቃላይ የሰላም እና የመልካም አሥተዳደር ሥራዎችም ተነስተው ምክክር እንደሚደረግ ተመላክቷል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!