የሴቶችን ተሳታፊነት እና ውሳኔ ሰጭነት ለማረጋገጥ እየተሠራ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

50

አዲስ አበባ: መጋቢት 20/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ከ100 በላይ ፕሮጀክቶችን አቅፎ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት እና ተራድኦ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ) የሴቶችን ተሳታፊነት እና ውሳኔ ሰጭነት ለማረጋገጥ በዓመት ከ56 ሚሊዮን በላይ የአሜሪካ ዶላር ወጭ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

የሴቶችን ወር ምክንያት በማድረግ በአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት እና ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስ ኤ አይ ዲ) የሚደገፉ የተለያዩ የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የሴቶች ቀንን በአዲስ አበባ አክብረዋል። በዩኤስኤአይዲ ኢትዮጵያ የሥርዓተ ፆታ አማካሪ መሰረት ካሳ ቀኑ ሲከበር ወደፊት ብዙ መሠራት እንዳለበት በማመን ነው ብለዋል፡፡

ሴቶችን በኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊ እና የፖለቲካ ዘርፎች ለማብቃት ሴቶችን ያማከለ ሁሉን አቀፍ አቀራረብ እና አካታች ሥራ መሠራት አለበት ነው ያሉት። ዩኤስኤአይዲ በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ የተለያዩ ፕሮግራሞች እና ፕሮጀክቶች የሴቶችን ተሳታፊነት እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሠራ እንደሚገኝም አማካሪዋ መሰረት ካሳ ተናግረዋል።

በዩኤስኤአይዲ ድጋፍ የሚደርጉ የተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የዓለም አቀፍ ድርጅት ሴት ተወካዮችን አቅም ማጎልበት በሚቻልባቸው ጉደዮች ላይ ውይይት አካሂደዋል።

ዘጋቢ፡- ቤቴል መኮንን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የሕዝብ ጥያቄዎች የደረሱበትን እንገመግማለን፤ የቀሩንን በአጭር ጊዜ ለመሥራት ልዩ ርብርብ እናደርጋለን” ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ.ር)
Next articleበአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ክልል አቀፍ ኮንፈረንስ እየተካሔደ ነው።