
ባሕር ዳር: መጋቢት 20/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በምዕራብ ጎጃም ዞን ሰከላ ወረዳ አርሶ አደሩ የአፈር ማዳበሪያ እየወሰደ ይገኛል። ደጋማ በኾነው አካባቢ ፈጥነው ለሚዘሩ ሰብሎች የአፈር ማዳበሪያ በማግኘታቸው አርሶ አደሮች ደስተኛ መኾናቸውን ተናግረዋል። ባለፈው ዓመት አጋጥሞ በነበረው የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት ችግር በዚህ ዓመትም በፀጥታ ችግሮች ላይቀርብ ይችላል በሚል ስጋት እንደነበረባቸው አርሶ አደሮቹ አስረድተዋል፡፡
የምዕራብ ጎጃም ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን መምሪያ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንዳሰፈረው በአካባቢው የተገኘውን አንፃራዊ ሰላም ዘላቂ በማድረግ ወደ መደበኛ የልማት እንቅስቃሴ ለመዞር የበኩላቸውን እንደሚወጡም አረጋግጠዋል፡፡ ከምዕራብ ጎጃም ዞን ለድጋፍ እና ክትትል ሥራ በስፍራው የተገኙ አመራሮች የቀረበውን የአፈር ማዳበሪያ በፍትሐዊነት እና በፍጥነት ለማሰራጨት የሚያደርጉትን ጥረትም አርሶ አደሮቹ አድንቀዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
