“ጽንፈኛ ኃይሎች ከአንድነታችን ለመነጠል የሚያደርጉት ሀገር የማፍረስ ተልዕኮ ተቀባይነት የለውም” የደጀን ወረዳ የየትኖራ ቀበሌ ነዋሪዎች

35

ባሕር ዳር: መጋቢት 20/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል የምሥራቅ ጎጃም ዞን ኮማንድ ፖስት አሥተባባሪ እና የኮር አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል አዘዘው መኮንን ከደጀን ወረዳ የትኖራ ቀበሌ ነዋሪዎች ጋር በሠላም እና ፀጥታ ዙሪያ እንዲሁም የአከባቢውን ደኅንነት ከማረጋገጥ አንፃር ውይይት አድርገዋል ።

በውይይቱ ወቅት ነዋሪዎቹ እንደተናገሩት ፀረ ሰላም ኃይሎች በሚነዙት ሽብር ከአንድነታችን በመነጠል ሀገር የማፍረስ ተልዕኮ ተቀባይነት እንደሌለው ተናግረዋል፡፡ ስኬታማ የሰላም ማረጋገጥ ሥራ በማከናወን የተገኘውን ለውጥ ለማስቀጠል ከሠራዊቱ ጎን በመቆም የሚጠበቅብንን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነን ብለዋል።

ብርጋዴር ጄኔራል አዘዘው በበኩላቸው ሕግን በመጣስ በሕዝብ እና ሀገር ላይ ሊፈጸም የሚችል የወንጀል ድርጊት እንዳይከሰት ለማድረግ ሠራዊታችን እና የክልሉ የፀጥታ ኃይል ምንጊዜም እስከመጨረሻው የደም ጠብታ መስዋእትነትን እንከፍላላን ብለዋል፡፡ ሠራዊቱ ሰላም የማስከበር ተልዕኮውን በአስተማማኝ ሁኔታ በመወጣት ሕዝባዊነቱን ያስመሠክራል ብለዋል።

ጽንፈኛው ቡድን በዞኑ ባሉ ወረዳዎች በጥፋት ተግባር ቢሰማራም ዓላማው እንዳይሳካ ለማድረግ ጠላትን እስከ መጨረሻው በገባበት ገብተን እርምጃ የመውሰድ ግዳጃችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።

በስብሰባው መርሐ ግብር ላይ የደጀን ወረዳ መሬት ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አስናቀ እይላቸው እና የየትኖራ ቀበሌ ሊቀመንበር ሞስዬ እንዳለ በፀረ ሰላም ኃይሎች ምክንያት ዞኑ ከነበረበት የሠላም እና የፀጥታ እንዲሁም ከፍተኛ ውድመት መውጣቱን ተናግረዋል፡፡ አሁን ላለበት አንፃራዊ ሰላም እንዲበቃ ያደረገው በቀጣናው የተሠማራው የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና የአማራ ፀጥታ ኃይል በመኾኑ ምሥጋና ይገባል ብለዋል።

የተገኘውን ለውጥ ለማስቀጠል እያንዳንዱ ነዋሪ የአካባቢውን ደኅንነት አስተማማኝ እንዲኾን እየተሠራ ባለው ሰላም የማስፈን ዘመቻ ከፍተኛ ፍላጎት ሊያሳይ እንደሚገባው አስገንዝበዋል።

መረጃዉ የጎጃም ኮማንድፖስት ነው፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየፓርቲያቸውን ተልዕኮ በመፈፀም የአካባቢያቸውን ሰላም ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እንደሚሠሩ የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ አባላት ገለጹ።
Next articleምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ተመስገን ጥሩነህ ሀገር አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ንቅናቄን አስጀመሩ፡፡