የፓርቲያቸውን ተልዕኮ በመፈፀም የአካባቢያቸውን ሰላም ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እንደሚሠሩ የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ አባላት ገለጹ።

26

ወልድያ: መጋቢት 19/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ፓርቲው በሁለት ዓመታት ውስጥ የሠራቸውን ሥራዎች፣ በኘሮግራሙ ያስቀመጣቸውን እና ከምርጫ ማግስት ለሕዝቡ ቃል የገባቸውን ጉዳዮች አፈፃፀም፣ ጥንካሬ እና ድክመት ስለመገምገሙ የአማራ ሕንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ታደሰ ግርማው ገልጸዋል።

የግምገማ ሃሳቦቹም በቀጣይ ተይዘው የሚፈፀሙበትን አቅጣጫ በማስቀመጥ ፓርቲውን እንደ ሀገር ለመገምገም እና ተሳታፊዎችን ለመምረጥ ታላሚ ያደረገ ስለመኾኑም አስረድተዋል። የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኀላፊ ዳዊት ብርሃኑ ባለፉት ሁለት ዓመታት የአባላቱ እና የአመራሩ ሚና ምን ነበር የሚለው ስለመገምገሙ ገልጸዋል፡፡

ሁሉም የየራሱን ድርሻ ወስዶ ፓርቲው ያስቀመጠውን ግብ ለማሳካት ርብርብ ማድረግ እንዳለበትም በኮንፈረንሱ መግባባት ላይ ተደርሷል ነው ያሉት። ከወቅታዊ ጉዳይ አኳያ ከቀበሌ እና ከክፍለ ከተማ ጀምሮ የፓርቲ አባላትን ማወያየታቸውን የገለጹት የአማራ ሕንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ታደሰ ግርማው ክልሉ ከገባበት ቀውስ እንዲወጣ ተጋግዞ መሠራት እንደሚያስፈልግ መግባባት ላይ መደረሱን አስረድተዋል።

የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የፓርቲውን ዓላማ የሚፈጸመው ከታችኛው መዋቅር ጀምሮ በመኾኑ የድርሻን መወጣት እንደሚገባ ነው የተናገሩት፡፡ የፓርቲውን ዓላማ ለማሳካትም እንደሚተጉ ነው የገለጹት። የአካባቢያቸውን ሰላም ለማስጠበቅ እንደ ፓርቲ አባል በትጋት እንደሚሠሩም ተናግረዋል።

ዘጋቢ፡- ካሳሁን ኃይለሚካኤል

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ወሰናችን ተከዜ ነውና ከትግራይ ሕዝብ ጋር በመልካም ጉርብትና እንኖራለን” የቆራሪት ከተማ ነዋሪ
Next article“ጽንፈኛ ኃይሎች ከአንድነታችን ለመነጠል የሚያደርጉት ሀገር የማፍረስ ተልዕኮ ተቀባይነት የለውም” የደጀን ወረዳ የየትኖራ ቀበሌ ነዋሪዎች