
አዲስ አበባ: መጋቢት 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ላለፉት ሦስት ወራት ሲካሂድ የቆየው ተረክ በኤም ፔሳ(M-PESA) የሽልማት መርሐግብር መጨረሻ የኾነው የስድስተኛው ዙር ሽልማት አሰጣጥ እና የመርሐግብሩ መዝጊያ ሥነ ሥርዓት በአዲስ አበባ አከናውኗል። የመርሐግብሩ መጨረሻ በኾነው 6ኛ ዙር ዕድለኞች ከሁለት መኪኖች በተጨማሪ ሦሥት ባጃጆች፣ 360 ስልኮች እና በሺህዎች የሚቆጠር የአየር ሰዓት ዕጣዎችን ተሸልመዋል ።
በተረክ የሽልማት መርሐግብሩ በአጠቃላይ አራት መኪኖች፣ 24 ባጃጆች፣ 2160 ስልኮች እና በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዋጋ ያለው የአየር ሰዓት ሽልማቶችም በስድስቱ ዙር ለባለዕድለኞች ተሸልመዋል። የኤም ፔሳ ሳፋሪኮም የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ስትራቴጂክ አጋርነት ክፍል ኀላፊ ክፍሌ ኃይለየሱሰ በመዝጊያ ሥነ ሥርዓቱ ላይ እንዳሉት ሽልማቶቹ የዕድለኞችን ሕይወት ከመለወጡ በተጨማሪ የገንዘብ ክፍያን እና ዝውውርን ያቀለለ፣ መተግበሪያውን ያስተዋወቀ እና የብራንዱን ታዋቂነት ከፍ ያደረገ መርሐግብር ነበር።
የኤም ፔሳ ደንበኞች 4 ነጥብ 2 ሚሊዮን የደረሰ ሲኾን መርሐ ግብሩ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ደንበኞች የተሸለሙበት እንደነበርም ተገልጿል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
