
ባሕር ዳር: መጋቢት 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ዛሬ ጠዋት በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት ሥራ ሂደት መገምገማቸውን ገልጸዋል። ቀዳሚ አላማችን አዲስ አበባ ለነዋሪዎቿ ኑሮ የተመቸች ሳቢ ከተማ ለማድረግ ያለንን ቁርጠኝነት ማሳካት ነው ብለዋል።
“የማልማት ሥራ ሂደቱ በግሉ ክፍለ ኢኮኖሚና በመንግሥት ብሎም አነስተኛ ገቢ ባላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች እና የተለያዩ አካላት የተያዙና የተከራዩ ንብረቶችን የነካ ሊሆን ቢችልም ይህ ለረዥም ጊዜ ፋይዳ ትልም ይዞ የተነሳ ሥራ ሲጠናቀቅ ለሁሉም ባለድርሻ አካል ብሎም ለሰፊው ሕዝብ የሚሰጠው ጥቅም ትልቅ ነው።” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባጋሩት መልእክት።
በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እንዳሉት እየተስተዋለ ያለው አዲስ የሥራ ባሕል ማቆጥቆጥ በመላው ሀገራችን ሊቀዳ እና ሊባዛ የሚገባው ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!