“ሁሉን ለማካተት እንነሳ” በሚል መሪ መልዕክት የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኛ ሴቶች ብሔራዊ ማኅበር ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን እያከበረ ነው።

36

አዲስ አበባ: መጋቢት 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኛ ሴቶች ብሔራዊ ማኅበር በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ113ኛ ጊዜ፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ48ኛ ጊዜ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በአዲስ አበባ እያከበረ ነው።

የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኛ ሴቶች ብሔራዊ ማኅበር ዋና ሥራ አስኪያጅ ድባቤ ባጫ የሴቶች ቀንን ስናከብር ጠንካራ እና ለስኬት የበቁ ሴቶችን ምሳሌ በማድረግ የአካል ጉዳተኛ ሴቶች ለስኬት እንዲበቁ ማበረታታት እና መደገፍ ያስፈልጋል ብለዋል።

ወይዘሮ ድባቤ በአሁኑ ሰዓትም ለብዙ የአካል ጉዳተኛ ሰዎች ሞት መንስኤ እየኾነ የመጣውን የትራፊክ አደጋ ለመከላከልም መንገዶች ሲሠሩ የአካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረጉ መኾን እንዳለባቸው ተናግረዋል። በመድረኩም አካል ጉዳተኛ ልጆቻቸውን ለመደገፍ ውድ ዋጋ ሰጥተው ለቁም ነገር ለማብቃት ለሚተጉ ወላጆች ዕውቅና እንደሚሰጥም ተናግረዋል።

ዘጋቢ፡- ቤቴል መኮንን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበሰሜኑ ጦርነት ጉዳት የደረሰበት የ013 ቦያ ቀበሌ ትምህርት ቤት ግንባታው ተጠናቅቆ ርክክብ ተደረገ።
Next article