
አዲስ አበባ: መጋቢት 17/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የባንኩ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የእለቱ የፕሬዚዳንቱ ተወካይ ኤፍሬም መኩሪያ ባንኩ የኮምፕሊያንስ ቀንን ማክበር ከጀመረ 3 ዓመት ማስቆጠሩንም ገልጸዋል፡፡ በዚህ ዕለትም ባንኩ በአሠራር ሂደት ውስጥ የባንክ መመሪያ እና መንገድ ጠራጊነት ስኬት እና ያጋጠሙት ችግሮች ገምግሟል።
አቶ ኤፍሬም ባንኩ የመንግሥት ባንክ ኾኖ የብሔራዊ ባንክን ተግባር ከከወነበት ከ1942 እስከ 1963 ያገለገለበትን ታሪክ ተጠቃሽ መኾኑን አንስተዋል፡፡ ራሱን ችሎ ባንክ ከኾነበት ከ1963 በኋላ ያለውን ሒደት በባንክ ታሪክ ተጠቃሽ መኾኑን ተናገረዋል።
የባንኩ የኮምፕሊያንስ ክፍል የኮምፕሊያንስ ቀንን ማክበር ከጀመረ 3 ዓመት ማስቆጠሩንም ገልጸዋል፡፡
አቶ ኤፍሬም በቅርቡ በአሠራር ጥሰት ያጋጠመው በአብዛኛው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተሳተፉበት የባንኩ ገንዘብ የመዝረፍ ሂደት አንዱ የሕግ ጥሰት መኾኑን በማሳያነት አንስተዋል። ይህም ባንኩ የውስጥ አሠራርን ከማስከበር ባለፈ በትውልድ ሥነ ምግባር ላይ መሥራት እንደሚጠበቅበት ያየበት መኾኑን ጠቅሰዋል።
የካፒታል ገበያ መቋቋምን ተከትሎ በገበያው ዋነኛ ተሳታፊ ለመኾን ቅድመ ዝግጅቶች ሲያደርግ የቆየ ባንክ መኾኑን አቶ ኤፍሬም ተናገረዋል። በገበያው ውስጥ ባንኩ እንዴት መሳተፍ እንደሚገባው በአግባቡ መገምገሙንም ነው ያነሱት።
ባንኮች ከካፒታል ገበያ ጋር ያላቸው ትስስርን በተመለከተ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።
ካፒታል ገበያ አክሲዮኖች፣ ኮንትራቶች እና ቦንዶች የሚለዋወጡበት የገበያ ሁነት ነው። በዚህም የካፒታል ገበያ መቋቋም እና ባንኮችም በዚህ መሳተፋቸው በዋናነት የሀገርን ኢኮኖሚ የሚደግፍ ነው ተብሏል።
ዘጋቢ፡- አንዱዓለም መናን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!