በጎጃም ኮማንድፖስት የተሰማራው ኮር በሰሜን ጎጃም ዞን እና በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ቀጠና 57 የጽንፈኛውን አባላት መደምሰሱን አስታወቀ።

29

ባሕር ዳር: መጋቢት 17/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኮሩ ዘመቻ ሻለቃ አረጋኸኝ አለሙ እንደተናገሩት የጽንፈኛው ታጣቂዎች በትናንትናው እለት በእብሪት ተነሳስተው ከባሕር ዳር ዙሪያ፣ ስናጊ፣ ብራቃት፣ ቢኮሎ ዓባይ፣ ዳጊ ከተባሉ የሰሜን ጎጃም አካባቢዎች ተሰባስበው ለሽብር ሲዘጋጁ ገርጨጭ ላይ መከላከያ ሠራዊት በወሰደው እርምጃ ቻላቸው ጌትነት የተባለው የጽንፈኛውን አመራር ጨምሮ 42ቱ ሲገደሉ 07 ተማርከዋል ።

በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ቹጋሌ ቀበሌ በኢንስፔክተር አስማማው ብርሃኔ የሚመራው የአማራ ክልል አድማ ብተና እና በአቶ ጌታቸው ቢሻው የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ሰላም እና ደኅንነት ኅላፊ የሚመራው የዞኑ ሚሊሺያ በጋራ በመኾን በወሰዱት እርምጃ 15 የጽንፈኛው ታጣቂዎችን መደምሰሳቸውንም አረጋግጠዋል ።

በዳንግላ ከተማ በተደረገው የሕዝብ መድረክ የተሰበሰበው ነዋሪ፣ እኛ ሰላም ነው የምንፈልገው ሲሉ ለሰላም ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል። ጽንፈኛው ለአማራ ሕዝብ የማይጠቅም መኾኑን የገለጹ ሲሆን በፀጥታ ችግሩ ንብረታችን ተዘርፈናል ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ ለቤተ ክርስቲያን የተዋጣ ገንዘብ ጽንፈኛው ዘርፏል ማለታቸውን ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበዓለም ላይ የሚገኙ ሀገራት ሙስና እና ብልሹ አሠራርን ለመከላከል የተለያየ አሠራር ይከተላሉ።
Next article“ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ኀላፊነትን በአግባቡ መወጣት ይገባል” የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር