
ባሕር ዳር: መጋቢት 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በአካባቢው የሚገኘው ክፍለጦር አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ሃብቱ ከበደ እንደተናገሩት ደብረ ማርቆስ ህልሙ የኾነችበት ፅንፈኛው ኀይል ከተማውን የሽብር አውድማ ለማድረግ በማሰብ በተለያየ አቅጣጫ ለመምጣት የሞከረውን ኀይል በአከባቢው ባሉት የመከላከያና የክልሉ የጸጥታ ጥምር ኀይል መመታቱ ተገልጿል።
በዚህ ስምሪት አስር የጽንፈኛዉ ቡድን አባላት ሲደመሰሱ 15 ቆስለዋል፤ አምስት በምርኮ ተይዘዋል። የአውቶማቲክና ቃታ መሳሪያዎች እንዲሁም ካዝናዎች ተማርከዋል ብለዋል ። ከተማረኩት መካከል መሰረት ቢያድግ እንደተናገረችው፣ ጽንፈኛው ቡድን አስገድዶ እንደሚያዋጋቸው ፣ ከዚያ ለመውጣትም ቤተሰቦቻቸውን ብር እንደሚያስከፍሉ ተናግራለች። የሷ ቤተሰቦች የተጠየቁትን ከፍተኛ ገንዘብ መስጠት ስላልቻሉ እሷ ከጽንፈኞቹ ጋር አብራ ስትንቀሳቀስ መቆየቷን ተናግራለች።
የደብረ ማርቆስ ከተማ ከንቲባ መንበሩ ዘውዴ ፅንፈኛው በውሸት ትርክቱ በተደጋጋሚ ገድያለሁ፣ ያልተቆጣጠረውን ተቆጣጥሪያለሁ በሚል የውሸት ስካር የተወናበደ ኀይል መኾኑን ሕዝቡ ከቀን ወደ ቀን እየተገነዘበው የመጣ መኾኑን ገልጸዋል። ደብረ ማርቆስ እንደተለመደው ፍጹም ሰላምዊ እንቅስቃሴ ላይ የምትገኝ ከተማ መኾኗን አረጋግጠዋል። የከተማው እና የአካባቢው ሕዝብም ጽንፈኛ ቡድኑ በሚለቃቸው የተለመዱ የውሸት ፕሮፖጋንዳዎች ሳይረበሽ የእለት ከእለት ኑሮዉን በተረጋጋ መንገድ እንዲቀጥል አሳስበዋል ።
መረጃዉ ጎጃም ኮማንድፖስት ነዉ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!