
ባሕር ዳር: መጋቢት 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጆሴ ማሲንጋ ጋር በአማራ ክልል ወቅታዊ የሰላምና የልማት ሥራዎች ላይ ውይይት አካሂደዋል።
በውይይቱም በአማራ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ይርጋ ሲሳይ እና የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ.ር) መገኘታቸውን ከአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!