ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ እንደሚገኝ የሰሜን ሸዋ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ።

23

ባሕር ዳር: መጋቢት 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ምርት እና ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ እንደሚገኝ የሰሜን ሸዋ ዞን ግብርና መምሪያ አስታውቋል፡፡ በዘኑ በ2016/2017 የምርት ዘመን ከ495 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር በመሸፈን ከ15 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዷል፡፡

የሰሜን ሸዋ ዞን ግብርና መምሪያ ምክትል ኀላፊ ሰለሞን ቀለሙ ለምርት ዘመኑ ስኬታማነት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ መኾኑን ገልጸዋል፡፡ ከቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ውስጥ የእርሻ ሥራ ቀዳሚው ተግባር መኾኑን ጠቁመዋል፡፡ እስካሁን ባለው እንቅስቃሴም ከ196 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት አንደኛ ዙር እርሻ መታረሱን አንስተዋል።

ምርታማነትን ለማሳደግም ከ1 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ሰው ሰራሽ የአፈር ማዳበሪያ ለማቅረብ ታቅዶ እየተሠራ ነው፡፡ እስካሁንም ከ656 ሺህ ኩንታል በላይ ሰው ሠራሽ ማዳበሪያ መቅረቡን ምክትል መምሪያ ኀላፊው አንስተዋል። በእቅድ የተያዘውን ምርት ለማሳካትም አረሶ አደሮችን በቴክኖሎጂ ማገዝ መቻሉን የገለጹት አቶ ሰለሞን ከ22 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በትራክተር መታረሱን ተናግረዋል። ቀጣዩን የመኸር እርሻ ውጤታማ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተሠሩ ሥለመኾናቸው ከመምሪያው የተገኘ መረጃ ይጠቁማል።

ዘጋቢ፡- ፋንታነሽ መሐመድ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሜጋቢት 15 ም.አ ቺርቤዋ ጋዚቲ
Next articleየኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሐጅ እና ዑምራ ተጓዦች የሚሰጠውን አገልግሎት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ።