የፌዴራል መንግሥት ሱፐርቪዥን ቡድን በአማራ ክልል ሲያካሂድ የቆየውን ልዩ የሥራ ድጋፍ እና ክትትል የማጠናቀቂያ መርሐ ግብር እያካሄደ ነው።

73

ባሕር ዳር: መጋቢት 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትሯ ጫልቱ ሳኒ የተመራው የፌዴራል ሱፐርቪዥን ቡድን በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የመልካም አሥተዳደር እንቅስቃሴዎችን ሲመለከት ቆይቷል። በክልሉ የሚካሄዱ የልማት ሥራዎችን በመመልከት ድጋፍ እና ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል። በተለይም የመስኖ፣ የሌማት ትሩፋት፣ የመንገድ መሰረተ ልማት ጉዳዮች የድጋፍና ክትትሉ ትኩረት እንደነበሩ ተገልጿል።

የሱፐርቪዥን አባላቱ ለአንድ ሳምንት ያህል ሲያካሂዱት ስለቆዩት የድጋፍ እና ክትትል ሥራ ግብረ መልስ በባሕር ዳር ከተማ እየሰጡ ነው። ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተው ግብረ መልሱን እያዳመጡ ነው፤ ውስንነቶችን ለማረም እና ጥንካሬዎችን የበለጠ ለማስፋት ጠቃሚ ሱፐርቪዥን ስለመኾኑም ተነስቷል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በኢትዮጵያ በኤሌክትሪክ ኀይል የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ቁጥር ከ100 ሺህ በላይ ደርሰዋል” የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር
Next articleበአማራ ክልል ውስጥ ሰላምን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ጠንካራ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መኾኑን የፌዴራል መንግሥት ሱፐርቪዥን ቡድን አባላት ገለጹ።