
ደብረ ብርሃን: መጋቢት 13/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የመርሐቤቴ እና የዓለም ከተማ አሥተዳደር የሥራ ኀላፊዎች በቀጣናው የፀጥታ እና የልማት ሥዎች ዙሪያ እየመከሩ ነው፡፡ በምክክር መድረኩ የቀጣናው ኮማንድ ፖስት ሠብሣቢን ጨምሮ የዞን የሥራ ኀላፊዎች እንዲሁም የሁለቱም የወረዳ የፀጥታ ምክር ቤት አባላት እየተሳተፉ ነው።
በምክክር መድረኩ ላይ የቀጣናውን የፀጥታ ኹኔታ አስተማማኝ ለማድረግ መግባባት ላይ ተደርሷል ነው የተባለው።
በቀጣይ በሚፈፀሙ አጠቃላይ ሰላምን የማጽናት ተግባራት ላይ ግልጽነት የተፈጠረበት መድረክ ስለመኾኑም ተመላክቷል። የሰላም እና የልማት ሥራዎች ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባም መገለጹንም የሰሜን ሸዋ ዞን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ያሰፈረው መረጃ ጠቁሟል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!