“በጎጃም ኮማንድ ፖስት ስር የሚገኘው ኮር የተሻለ ግዳጅ ለመፈጸም ራሱን ማዘጋጀት አለበት” ብርጋዴር ጀኔራል አዘዘው መኮንን

49

ባሕር ዳር፡ መጋቢት 12/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ኮሩ ከክፍለጦር እና ከሬጅመንት አመራሮች ጋር እስካሁን ያደረጋቸውን ስምሪቶች ገምግሟል። በግምገማው የተገኙት ብርጋዴር ጀኔራል አዘዘው መኮንን እንደተናገሩት ኮሩ በአማራ ክልል በምስራቅ ጎጃም ዞን በመሠማራት የጽንፈኛ ቡድኑ ላይ እርምጃ በመውሰድ ለሕዝቡ ሰላም ማስገኘት ተችሏል ብለዋል።

የኮር ሬጅመንቶች በተሰማሩበት ዋና ዋና የግዳጅ ቀጣና በተለይም በቁይ፣ በየጁቤ፣ በሸበል፣ በደብረ ወርቅ፣ በግንደወይን፣ በመርጡለ ማርያም፣ በሰኞ ገበያ፣ በጉብያ ዙሪያ (በደጀን ወረዳ የምትገኝ)፣ በአንበር፣ በሉማሜ እና በብቸና ዙሪያ ኦፕሬሽን በማካሄድ ፅንፈኛውን ከጥቅም ውጭ ማድረግ ችለዋል። በርካታ የጦር መሳሪያም በቁጥጥር ስር አውለዋል ተብሏል።

ብርጋዴር ጀኔራል አዘዘው እንዳሉት የሀገር እና የሕዝብን ሰላም መጠበቅ የምንችለው ያለንን ዝግጁነት በማረጋገጥ እና ግዳጅን አጠናክሮ ማስቀጠል ሲቻል መሆኑን በመረዳት በኮሩ ስር የሚገኙ አመራሮች ባከናወኑት ፀረ -ሰላሞችን የገቡበት ገብቶ የመደምሰስ ዘመቻ አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን አረጋግጠዋል።

በቀጣናው ሰላም የማስፈን የኅብረተሰቡን ደኅንነት የመጠበቅ እና ሕግ የማስከበር ግዳጅን በብቃት በመፈጸም በኮሩ ስር የሚገኙ አመራሮች የሚጠበቅባቸውን ሁሉ መፈፀም እንደሚገባቸው የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል። መረጃው የጎጃም ኮማንድ ፖስት ነዉ።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article”የከተሞች ችግር መዋቅር በመዘርጋት እና ቴክኖሎጂ በመጠቀም ብቻ አይፈታም” የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ
Next articleከምጥ በላይ የሰላም እጦት የፈተናቸው እናት!