“ኢማን ኢስላሚክ አሶሴሽን” ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረገ።

21

ደሴ: መጋቢት 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ከተለያዩ ቦታዎች ተፈናቅለው በሀርቡ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ወገኖች የረመዷን ጾምን ምክንያት በማድረግ “ኢማን ኢስላሚክ አሶሴሽን” የተሰኘው እስላማዊ ማኅበር ለተፈናቃይ ወገኖች የምግብ ግብዓቶችን ድጋፍ አድርጓል።
የኢማን ኢስላሚክ አሶሴሽን የአሥተዳደር እና ፋይናንስ ክፍል ኀላፊ ሀይደር አብዱ ድጋፉ ከ500 ሺህ ብር በላይ ወጭ እንደተደረገበት ገልጸዋል፡፡

ማኅበሩ ወገናዊ ኅላፊነቱን ከመወጣት አንጻር ከዚህ በፊት በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ለሚገኙ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የተለያዩ ድጋፎች ሲያደርግ መቆየቱንም አስታውሰዋል፡፡ ዛሬ በሀርቡ ከተማ የተደረገው ድጋፍም በሌሎች የመጠለያ ጣቢያዎች ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ድጋፉን የተረከቡት የሀርቡ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ያሲን አመዴ በመጠለያ ጣቢያው ከ1ሺህ 500 በላይ የሚኾኑ ተፈናቃይ ወገኖች እንደሚኖሩ ተናግረዋል፡፡

ከንቲባ ያሲን “ኢማን ኢስላሚክ አሶሴሽን” ከ100 በላይ ለሚኾኑ አባወራዎች ጾሙን ምክንያት አድርጎ ያደረገው ድጋፍ ለወገኖቹ ያለውን አለኝታነት ያሳየበት ነው ብለዋል።ሌሎችም ድጋፍ በማድረግ ወገናዊ ኀላፊነትን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖችም ለተደረገላቸው ድጋፍ አመሥግነዋል።

ዘጋቢ፡- ማህሌት ተፈራ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ሀገር ያለ መንግሥት፣ መንግሥት ያለ ግብር ሕልውና የላቸውም” የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ
Next articleጽንፈኛው እና ዘራፊው ቡድን በፈጠረው ችግር ምክንያት በመሬት አሥተዳደር ሥርዓቱ እና በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ ጉዳት መድረሱን የአማራ ክልል መሬት ቢሮ ገለጸ።