
ባሕር ዳር: መጋቢት 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ከግሪክ አቻቸው ጋር መክረዋል።የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ከግሪክ ፕሬዚዳንት ካትሪና ሳኬላሮፖሉ መኖሪያ ቤት ተገኝተው ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና ግሪክ መካከል ያለውን ታሪካዊ የወዳጅነት እና የትብብር ትስስር በድጋሚ አረጋግጠዋል። ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ኢትዮጵያ እና ግሪክ የቆየ የሁለትዮሽ ግንኙነት እንዳላቸው ገልጸዋል። ግንኙነቱን ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የግሪክ ፕሬዚዳንት በበኩላቸው ኢትዮጵያውያን በግሪክ እንደሚኖሩ ሁሉ ለብዙ አስርት ዓመታት የግሪክ ማኅበረሰብ በኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚኖር አንስተዋል፡፡ አክለውም ዲያስፖራው በሀገራቱ መካከል ያለውን የወዳጅነት ትስስር እና ትብብርን የሚያጠናክር ድልድይ ኾኖ በባሕል እና የተለያዩ መስኮች እየሠራ እንደሚገኝም ነው ያነሱት፡፡
ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በአቴንስ እየተካሄደ ያለውን የሴቶች ፖለቲካ መሪዎች ጉባኤ ምክንያት በማድረግ በግሪክ ይገኛሉ።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!