
ደሴ: መጋቢት 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የደሴ ከተማ አሥተዳደር በወቅታዊ የጸጥታ እና ደኀንነት ጉዳይ በከተማ አሥተዳደሩ ከሚገኙ የግል እና የመንግሥት ትምህርት ቤት መምህራን ጋር ምክክር እያካሄደ ነው፡፡
በመድረኩ ምክትል ርእሰ መሥተዳደር አብዱ ሁሴን፣ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ እና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ.ር)፣ የደቡብ ወሎ ዞን እና የደሴ ከተማ አሥተዳደር ኮማንድፖስት ሠብሣቢ ብርጋዴል ጄኔራል ዘውዱ ሰጣርጌን ጨምሮ የተለያዩ የክልል እና የከተማ አሥተዳደሩ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በምክክር መድረኩ በክልሉ ወቅታዊ የጸጥታ እና ደኅንነት ዙሪያ የተለያዩ ሃሳቦች ተነስተው ማብራሪያ እንደሚሰጥባቸው ይጠበቃል፡፡
ዘጋቢ፡- ደጀን አምባቸው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!