የፌዴራል መንግሥት የሱፐርቪዥን ቡድን አባላት በደቡብ ወሎ ዞን ያሉ የልማት ሥራዎችን ተመለከቱ።

14

ባሕር ዳር: መጋቢት 10/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ.ር) የተመራው የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ያካተተው የልዑካን ቡድን አባላት በዞኑ ውስጥ ሕዝብን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን ምልከታ በማድረግ ላይ ይገኛል።

በዛሬው ዕለት በአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ ደለመኔ ሞዴል ተፋሰስ ውስጥ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸውን ችግኞች በመትከል ለወጣቶች የሥራ ዕድል የተፈጠረበትንና ሕዝብን ተጠቃሚ ያደረጉ የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ውጤቶችን ተዘዋውረው መመልከታቸውን ከዞኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየምስራቅ አማራ ኮማንድ ፖስት በወቅታዊ ጉዳዮች እና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት እያደረገ ነው።
Next article“የዓድዋ ድል መታሰቢያ የኢትዮጵያዉያንን ማንነት የሚገልጽ ጥልቅ የሀገር ሀብት ነው” ሼህ አብዱላዚዝ አብዱልዋሊ