
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 10/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በመድረኩ የደቡብ ወሎ እና ሰሜን ወሎ ዞኖች፣ የደሴ፣ ወልዲያ እና ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደሮች፣ የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር፣ የከተማ እና የወረዳ የሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች እና የጸጥታ አመራሮች እንዲሁም የሀገር መከላከያ ሠራዊት አዛዦች ተገኝተዋል።
መድረኩ የአካባቢውን ሰላም ዘላቂ በማድረግ ረገድ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን በዝርዝር በመገምገም በቀጣይ ጊዜያት ተግባራዊ የሚደረጉ አቅጣጫዎችን ያመላክታል ተብሎ ይጠበቃል።
ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን፣ የርእሰ መሥተዳድሩ የአደረጃጀት ዘርፍ አማካሪ ፍሰሃ ደሳለኝ፣ የርእሰ መሥተዳድሩ የሕዝብ ግንኙነት አማካሪ ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ.ር )፣ የሰሜን ምሥራቅ እዝ አዛዥ ሌተናል ጀነራል አሰፋ ቸኮል እና ሌሎች የክልል ከፍተኛ መሪዎች ተገኝተዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!