የሸዋ ኮማንድፖስት በሰላም እና ጸጥታ ዙሪያ የተከናወኑ ዓበይት ተግባራትን እየገመገመ ነው።

18

ባሕር ዳር: መጋቢት 10/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የሸዋ ኮማንድፖስት በሰላም እና ጸጥታ ዙሪያ የተከናወኑ ዓበይት ተግባራትን በደብረ ብርሃን ከተማ እየገመገመ ነው፡፡

የሰሜን ሸዋ ዞን ወረዳዎች እና የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር በጋራ ምክክር እያካሄዱ ባለበት በዚህ መድረክ በአማራ ክልል በምክትል ርእሰ መስተዳደር ማዕረግ የከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አሕመዲን መሐመድ (ዶ.ር) ጨምሮ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር እና የሰሜን ሸዋ ዞን የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች መገኘታቸው ተገልጿል፡፡

የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ አዛዥ እና የሸዋ ኮማንድፖስት ዋና ሰብሳቢ ሌተናል ጀኔራል ሹማ አብደታ እንዳሉት የግምገማው ዓላማ ሕዝቡን በፍጥነት ወደ ሰላሙ ለመመለስ የተከናወኑ እና ወደፊት መከናወን ስላለባቸው የልማት እና የሰላም ሥራዎች ላይ መወያየት ነው።

በመድረኩ የልማት እና የሰላም አጀንዳዎችን አቀናጅቶ ከመምራት አኳያ ያጋጠሙ ፈተናዎችን እና ጠንካራ ተግባራትን የሚፈተሹ እንደኾነም ተመላክቷል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየዲዛይን ቁጥጥር እና ክትትል ሥራዎች በተቀናጀ መንገድ በመሥራት የመስኖ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እና ገንዘብ እንዲጠናቀቁ መሥራት እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ።
Next articleበጎንደር ከተማ ፖለቲካዊ፣ ምጣኔ ሃብታዊ እና ማኅበራዊ እንቅስቃሴዎች አፈጻጸም ዙሪያ ምክክር ተካሄደ።