ለበርካታ ሥራ አጥ ወጣቶች የሥራ እድል መፈጠሩን የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ሥራ እና ሥልጠና መምሪያ ገለጸ።

8

ባሕር ዳር: መጋቢት 10/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በመምሪያው ለ9 ሺህ 624 ወጣቶች የሥራ እድል ለመፍጠር ታቅዶ ነበር ያሉት የመምሪያው ኀላፊ ዓለምነህ ጌጤ በጸጥታ ችግር ምክንያት ተንቀሳቅሶ ሥራ አጦችን ለመለየት እና ለመመዝገብ አዳጋች ኾኗል ብለዋል። የተለዩትንም ወደ ሥራ ለማስገባት ጸጥታው እንቅፋት መፍጠሩን ነው የገለጹት።

በመኾኑም በስድስት ወር አፈፃፀም 5 ሺህ 800 በላይ ሥራ አጦችን በመለየት ከ2 ሺህ 800 በላይ ለሚኾኑት ሥራ አጦች በኢንዱስትሪ፣ በከተማ ግብርና እና በአገልግሎት ዘርፍ የሥራ እድል እንደተፈጠረላቸው አስረድተዋል።

ለንብ እርባታ 10 ሚሊዮን ብር ለዶሮ እርባታ ደግሞ 14 ሚሊዮን ብር በጀት በመመደብ የቀፎ እና የዶሮ መጠለያ ግንባታዎች እንዲሠሩ፣ ወጣቶቹም ሥልጠና እና ብድር የሚያገኙበትን መንገድ መመቻቸቱን ገልጸዋል።

አኹን ያለውን አንፃራዊ ሰላም በመልካም አጋጣሚ በመጠቀም በቀሪ ወራት ቀሪ ሥራዎችን በመከወን ለሌሎች ሥራ አጥ ወጣቶች የሥራ እድል ለመፍጠር መምሪያው ይሠራል ብለዋል።

ዘጋቢ:- ካሳሁን ኃይለሚካኤል

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበፌዴራል መንግሥት እየተሠሩ ያሉ ፕሮጀክቶች ባለመጠናቀቃቸው በኅብረተሰቡ ዘንድ ቅሬታ እያስነሱ መኾናቸው ተገለጸ።
Next articleያልተጌጠበት ነጭ ወርቅ!