የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ልዑክ በደቡብ ወሎ ዞን የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን ምልከታ አደረገ።

20

ባሕር ዳር: መጋቢት 9/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ.ር) የተመራው የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎችን ያካተተው ልዑክ በደቡብ ወሎ ዞን የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን ምልከታ አድርጓል።

በሀገራችን ሁሉም አካባቢዎች የተከናወኑ የልማት እና መልካም አሥተዳደር ሥራዎች የመስክ ምልከታ እና ድጋፋዊ ክትትል በፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ቡድን እየተካሄደ ይገኛል።

መንግሥት በሀገር ደረጃ በሁሉም ክልሎች ያሉ ሃብቶችን እና ጸጋዎችን በአግባቡ ለመጠቀም እንዲቻል እና የሚነሱ ቅሬታዎችንም ከኀብረተሰቡ ጋር ተቀራርቦ ለመፍታት እየሰራ ነው ተብሏል። የድጋፋዊ ሱፐርቪዥን መርሐ ግብሩም የዚህ ተግባር አንድ አካል ስለመኾኑ ተጠቁሟል።

የፌደራል መንግሥት የሱፐርቪዥን ልዑካን ቡድንም በደቡብ ወሎ ዞን የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን ምልከታ አድርጓል። በምልከታው በዞኑ ውስጥ የተከናወኑ የበጋ መስኖ ሥንዴ ልማት፣ የተፈጥሮ ሃብት ልማት እና ጥበቃ ሥራ፣ የሌማት ትሩፋት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና ሌሎች የልማት ሥራዎችን ያካተተ ነው ተብሏል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleከ404 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ብሔረሰብ አሥተዳደሩ መግባቱን የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ግብርና መምሪያ አስታወቀ።
Next articleኢትዮጵያ እና ስዊዘርላንድ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ማጠናከር በሚያስችላቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ።